ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ የክትትልና ድጋፍ ተግባራትን ያከናውናል:: ለተማሪው የሚያስፈልጉ ነገሮች እንዲሟሉም ጥረት ያደርጋል:: ዩኒቨርሲቲው ብቃት ያላቸውን መምህራን በመመደብ የሚሰጠው ትምህርት የጥራት ደረጃውን ለመጠበቅ የተለያዩ ጥረቶች እንደሚያደርግም አዲሱ ይናገራል::
አዲሱ አያይዞም “የትምህርት አሰጣጥ ጥራትን ለማስጠበቅ ዩኒቨርሲቲው የሚያደርገው ከሚያደርጋቸው ዘርፈ ብዙ ጥረቶች መካከል በተከታታይና በማጠቃለያ የሚሰጡ ፈተናዎች ደረጃቸው የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ ተማሪዎች ይህንን አውቀው በቂ ጥናትና ዝግጅት እንዲያደርጉ ያበረታታል፡፡“ ይላል::