ዩኒቨርሲቲው ስራ አጥነትን በመቅረፍ ረገድ ድርሻውን እየተወጣ መሆኑ ተገለጸ

አድማስ ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ በቢሸፍቱና በመቐለ በሚገኙ ካምፓሶቹ  ለ1 ሺሕ 1 መቶ 41  ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን አስታወቀ።    

የዩኒቨርስቲው የአስተዳደርና ፋይናንስ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን አማረ እንደገለጹት  ዩኒቨርስቲው ያለው የሰው ሃይል በየጊዜው ከፍና ዝቅ የሚል ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት  769 ቋሚና 372  የትርፍ ሰዓት መምህራን ዩኒቨርስቲው የፈጠረውን የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል።

አቶ ካሳሁን አያይዘውም አድማስ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎችና እርከኖች የተማረን የሰው ሃይል ከማፍራት ባኛገር ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ረገድም ቀላል የማይባል ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው ከተለያዩ ተቋማት ጋር የጠበቀ ግንኙነት በማድረግ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በቀላሉ የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው እያደረገ ይገኛል፡፡

አድማስ ዩኒቨርስቲ አይ ኤስ ኦ (ISO) ሰርቲፊኬት ለማግኘት የሚያስችል ስራ እየሰራ

አድማስ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጲያ የጥራት ደረጃ ኤጀንሲ የተዘጋጁት ስታንዳርዶች በተገቢው መልክ በመፈፀም በ2012 ዓ/ም በተቋም ደረጃ አይ ኤስ ኦ (ISO) ሰርቲፊኬት ለማግኘት የሚያስችለውን ተግባራት  እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።

የዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ብሩ አስማረ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው የትምህርት አሰጣጥ ጥራት ደረጃውን በማሳደግ ለዚሁ ተገቢ የሆነ እውቅና ለማግኘት የሚያስችለው ብቃት ላይ ይገኛል።

በቴክኒክና ሙያ ኮሌጀች የትምህርት ሥልጠና ጥራት ለማስጠበቅና   በየሙያ ደረጃው የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ አድርጓል ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ  የማስልጠኛ መሳሪያዎች (TTLM) ዝግጅት በሁሉም የብቃት አሃዶች ማዘጋጀቱንና የትብብር ሥልጠናን አፈፃፃምን የሚያሻሻሉ  የተለያዩ ተገባራት እያከናወነ መሆኑን ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋክል።      

አቶ ብሩ አያይዘውም  የምዘና ሥርዓቱን  ለማጠናከርና በዩኒቨርስቲው የሚተገበረውን የተከታታይ   ማጠቃለያና ተቋማዊ ምዘና   ዝግጅትና አፈፃፃም ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን መደረጉንም አስረድተዋል።

በኢትዩጵያ የደረጃ ኤጀንሲ (Ethiopia Standard Agency )የተዘጋጅ   ስተንደርዶችን ማለትም  የስርዓተ ትምህርት (Curriculum Requirement  ES. 6259-1 : 2018) ፣

የመሳሪያዎች ማሽነሪዎች( Tools machines & Equipment requirement ES 6259-8 : 2018)፣  የምዘናና የማሰልጠኛ መሳሪያዎች (Assessment & Instructional Materials ES 6299-9: 2011 ) እና የመሳሰሉትን   ተግባራዊ እያደረገ ፡መሆኑን አቶ ብሩ ገልጸዋል፡ ምክትል  ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም በዩኒቨርሲቲው የሚስጠውን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና በምርምር ለማገዝ እንዲቻል የተለያዩ  ጥናቶች በማካሄድ  ያሉ ችግሮችን የመለየት ስራ በየጊዜው እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Admas University Mekelle Campus celebrates Women’s Day

Gender and saving clubs of Admas University Mekelle Campus has celebrated Women’s Day on March 8, 2019. 

They celebrated the Day under the theme of ‘Peace and synergy for women’s participation and benefits’.

It was celebrated colorfully in verities of performing activities aimed to promote the roles of women in the socioeconomic affairs of the society.

The staff and students of the university, academicians and higher officials including the Head of Zonal Women’s Office as well as invited guests have attended the celebration. 

Participants of the celebration not only visited one of the needy mothers nearby and donated   her in kind and in cash but also encouraged top female students as well as awarded teachers who devoted their time and money to support female students.

Participants visiting a needy mother at her home

There was also a briefing to the participants on the benefits of saving by bank professionals.

Bank workers addressing female students the benefits of saving

It is also learnt that the university students have also donated blood.

ተመራቂዎች በአገሪቱ የለውጥ እንቅስቃሴ በመሳተፍ አገራቸውን ማገልገል እንዳለባቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) – ተመራቂዎች በአገሪቱ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፍ እራሳቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውንና አገራቸውን ለማገልገል በታማኝነት መሳተፍ እንዳለባቸው የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሞላ ጸጋይ ገለጹ፡፡

አድማስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 358 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪና በቴክኒክና ሙያ አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሞላ ጸጋይ በምርቃው ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው በአገሪቱ ብቁ የሰው ኃይል በማምረት የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

ተመራቂዎች በአገሪቱ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፍ አገራቸውን ለማገልገል በታማኝነት መሳተፍ አለባቸውም ብለዋል።

በዩኒቨርሲቲው እየሰለጠኑ የሚገኙ ተማሪዎች ለአገሪቷ ዕድገት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ተቋሙ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎች በበኩላቸው ባገኙት እውቀት አገራቸውን ለማገልገል እንደተዘጋጁ ተናግረዋል።

ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ወጣት ጽጌብርሃን ስንታየሁ በኢትዮጵያ ያለው ለውጥ ለስራ የሚያነሳሳና ተስፋ የሚሰጥ በመሆኑ የበለጠ አስዋጽኦ ለማበርከት እንደሚያግዘው ተናግሯል።

ሌላዋ ተመራቂ ተማሪ እየሩሳሌም አስናቀ በበኩሏ ባገኘችው ዕውቀት ለመስራትና አገሯን ለማገልገል ዝግጁ መሆኗን ተናግራለች።

በገበየችው እውቀት ለመስራት አልያም የራሷን ስራ ፈጥራ ለመስራት እንደምትፈልግም ተናግራለች።

ከተመራቂዎቹ መካከል ከ2 ሺህ 300 በላይ በዲግሪ፣ 5 ሺህ 53 ደግሞ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት መርኃ ግብሮች የሰለጠኑ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ከ60 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ተገልጿል።

አድማስ ዩኒቨርሲቲ ከ7 ሺ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

ዳግም ከበደ

አዲስ አበባ (አዲስ ዘመን) – አድማስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ በሚገኙ ካምፓሶቹ በዲግሪ እና በቴክኒክ ሙያ ትምህርት እና ስልጠና መርሃ ግብሮች 7ሺ 358 ተማሪዎችን ትናንት አስመርቋል።

ተማሪዎቹ በአካውንቲንግ፣ በኮምፒውተር ሳይንስ፣ በቢዝነስ ማኔጅመንት እና በሌሎች ትምህርቶች የተመረቁ ናቸው።

በኮኮብ አዳራሽ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሞላ ፀጋይ የተማሪዎቹን መመረቅ አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት፤ ዩኒቨርስቲው ላለፉት 19

ዓመታት በአገሪቷ የልማት እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን የተማረ የሰው ሃይል በማሰልጠን ረገድ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።  ዘንድሮም ከ7 ሺ በላይ ተማሪዎች ከ1 ኛው ገጽ የዞረ ተመርቀዋል።

«ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ጥራቱን ከምንግዜውም በላይ ለመጨመር፤ በጥናት እና ምርምር ላይ አስተዋዕፆ ለማበርከት እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ያለውን ብርቱ እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥላል» ያሉት ፕሬዚዳንቱ የዘንድሮው ተመራቂዎች፤ በተመረቁበት የሙያ ዘርፍ አገራቸውን በጥሩ ስነ ስነምግባር ማገልገል እንዲችሉ አሳስበዋል።

ዩኒቨርስቲው ባለፉት 19 ዓመታት በመደበኛ እና በርቀት ትምህርት፤ በዲግሪ፣ በዲፕሎማ በሰርተፍኬት ከ60 ሺ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል። በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት በዲግሪ እና በቴክኒክ ሙያ በመደበኛውና በርቀት

ትምህርት በአገር ውስጥ እና በውጪ አገራት ( በሱማሌ ላንድ እና ፑንት ላንድ ) ከ30 ሺ በላይ ተማሪዎችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል።

ለአምስት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ዲኖች ሽልማት ተሰጠ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ቢሮ በየዓመቱ በሚያደርገው የሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን፣ በከተማይቱ ከሚገኙ 75 የግል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በላቀ አፈጻጸማቸው ለተመረጡ አምስት የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች ዲኖች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ፡፡

የማበረታቻ የምስክር ወረቀት ከገንዘብ ሽልማት ጋር የተቀበሉ ዲኖች የመገናኛ፣ የመስቀል፣ የምስራቅ፣ የመካኒሳ እና የቃሊቲ ካምፓስ ዲኖች በቅደም ተከተል አቶ አህመድ ሰይድ፣ አቶ አቡበከር አብዱ፣ አቶ ጥበበሥላሴ ተክለማርያም፣ አቶ አምሳሉ ቶማስ እና አቶ ናትናኤል ስዩም መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የቴክኒክና ሙያ ም/ፕሬዚደንት አቶ ብሩ አስማረ ገልጸዋል፡፡

በሽልማት ሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ሽልማቱን ለዲኖቹ በመስጠት ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ሞላ ፀጋይ በየዓመቱ ለሚደረገው ሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ለሌሎች ካምፓሶች ልምድ በማካፈል ሁሉም ካምፓሶች ተመሳሳይ ደረጃ ላይ እንዲገኙ ላደረጋችሁት ጥረት ምስጋና ይገባል ብለዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ አያይዘውም በቀጣይም የዓመቱን የምዘና ዕቅድ በማሳካት የእውቅና እድሳትና የምዘና የምስክር ወረቀት ካምፖሶቹ እንዲያገኙ የተጀመሩ ሥራዎችን በከፍተኛ ኃላፊነት እንደሚወጡ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከተሸላሚዎች መካከል የመገናኛ ካምፓስ ዲን አቶ አህመድ ሰይድ ለፍኖተ አድማስ እንደተናገሩት የማበረታቻ ሽልማቱ የበለጠ ለመስራት እንደሚያግዝ ጠቁመው ይህ ዓይነቱ ማበረታቻ በአድማስ በየዓመቱ ሲፈጸም የነበረ ሲሆን የዘንድሮው ለየት የሚያደርገው በአዲስ አበባ ከሚገኙ የግል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር ተወዳድረን ባገኘነው ከፍተኛ ውጤት በመሆኑ በጣም አስደሳች ነው ብለዋል፡፡

አቶ አህመድ አያይዘውም ለቀጣይ የተሻለ ሥራ እንዲሰራ ያደርጋል፣ የካምፓሱን ሰራተኞች መምህራንና ተማሪዎችን ብርታትና ጥንካሬ ያጠናክራል፣ ይህንን በቋሚነት እየፈፀሙ ላሉ ኃላፊዎችም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ቢሮ በከተማው ባሉ 75 የግል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በአርአያነት ከመረጣቸው ስድስት ኮሌጆች መካከል፣ አምስቱ የአድማስ ዩኒቨርሲቲ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ቴክኒክና ሙያ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ብሩ አስማረ ለፍኖተ አድማስ እንዳስታወቁት ቢሮው በአዲስ አበባ መስተዳድር የሚገኙ የግል የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችን የትምህርት ጥራትና የሰልጣኝ ተማሪዎች ብቃት ያረጋግጣሉ ያላቸውን የምዘና መስፈርቶች ተጠቅሞ በመገምገም ስደስት ኮሌጆችን በመጀመሪያ ደረጃ የመረጠ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አምስቱ የአድማስ ዩኒቨርሲቲ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ኮሌጆቹ በቅድመ ዝግጅት፣ በትግበራና በድህረ ምረቃ ባላቸው አጠቃላይ እንቅስቃሴና ውጤታማነት መገምገማቸውን የገለጹት ምክትል ፕሬዚደንቱ አምስቱም የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች የመመዘኛ ነጥቦቹን በተገቢው ሁኔታ በማሟላታቸው ሁሉም መመረጥ ችለዋል፡፡

መስፈርቶቹ የመመሪያና ደንብ አፈጻጸም፣ መረጃ አያያዝ፣ የአሰልጣኞች ብቃት፣ የምዘና ሥርዓትና አተገባበር፣ ተቋማዊ አቅምና በድህረ ምረቃ ያላቸውን የገበያ ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ሲሆን አምስቱም ኮሌጆች በመስፈርቶቹ መሰረት ከፍተኛ ደረጃ መመደባቸውን አቶ ብሩ አስረድተዋል፡፡

ም/ፕሬዚደንቱ አያይዘውም ምንም እንኳን የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይና ሰፊ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን በጀት በመመደብ የኮሌጆቹን አደረጃጀት፣ የትምህርት ግብዓቶችና ብቃት ያላቸውን አሰልጣኞች በማሟላት ለዚህ ውጤት መብቃቱን አክለው ገልጸዋል፡፡

ኮሌጆቹ ለውጤት ያበቃቸውን አጠቃላይ የሥራ ክንውን ወደ ሌሎች የግል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንዲስፋፉ ለማገዝም የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ባዘጋጀው የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም ከ 75 ኮሌጆች የተውጣጡ አመራሮች ካምፓሶቹን እንዲጎበኙ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በዚሁ መሰረት የመካኒሳና የመገናኛ ኮሌጆች መጎብኘታቸውን የገለጹት አቶ ብሩ ጎብኝዎቹ ያዩትን አጠቃላይ ሁኔታ አድንቀው ተሞክሮውን ወደየተቋማቸው ወስደው ለመተግበር እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

ም/ፕሬዚደንቱ አያይዘውም ተማሪዎች በድህረ ምረቃ ወቅት ሥራ እንዲያገኙ ለማገዝ ዩኒቨርሲቲው የተመራቂ ተማሪዎችና ማህበረሰብ ቢሮ በማቋቋምና በማደራጀት በየዓመቱ በተለያየ የትምህርት መስክ የሚመረቁ ተማሪዎች ከተለያዩ ተቋማት ጋር ግንኙነት በማድረግ እገዛ በማድረግ ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

The IFRS training has started today At Admas Olympia Campus 28/02/2018

The IFRS training has started today
**************
Last time, we have announced that International Financial Reporting Standards (IFRS) training will be given to Admas University regular students freely.
Currently the training is going on. More than 400 students are participating and 8 professional trainers from Admas University and external institutions are giving the training.
It is expected to be finalized within 40 hours till March 9, 2018.